Top Songs By Habesha Music
Credits
AUSFÜHRENDE KÜNSTLER:INNEN
Habesha Music
Künstler:in
Madingo Afework
Künstler:in
KOMPOSITION UND LIEDTEXT
Habesha Music
Songwriter:in
Yilma G/Ab
Songwriter:in
Elias Woldemariam
Songwriter:in
Lyrics
ተንገበገበልሽ አረረልሽ ሆዴ
አትራቂኝ በኔ ሞት አይብዛ መንደዴ
ያስታርቀን መውደዴ
ልመናዬን ስሚ ይቅርታሽ ይድረሰኝ
ጥፋቴን ለመርሳት እኔ አቅም አነሰኝ
ልቤ እየወቀሰኝ
ከትዝታሽ ንዳድ አልዳነም አንጀቴ
አንቺን ካጣሁ ወዲህ ተጨንቋል ስሜቴ
አልበላም አልጠጣም እምቢ እያለኝ ሆዴ
በይግባኝ ሳይታይ ሊቀር ነው ወይ ፍርዴ
የእድሜን ጠዋት ማታ በትካዜ ገፋው
አጣሁት ሰላሜን አንቺን ስላስከፋው
ያለውን ችያለው መጪው ካልከበደኝ
ጸልይልኝ ፍቅርሽ እንዳያሳብደኝ
ላንቺ ይብላኝ እንጂ አልል አልተመቸኝ
ላንቺ ይብላኝ እንጂ አልል አልተመቸኝ
እወዳታለው ማለት አይሰለቸኝ
እወዳታለው ማለት አይሰለቸኝ
ተራዬን ብነሳ ልበር እንደ ግዴ
ብመርጠው መራቁን አይቀናኝ መንገዴ
ስቴጂ ቢከፋኝ ስሞታ አላሰማ
ተለየሽኝ ብዬ ዛሬ አንቺን አላማ
ክፉሽን አውርቼ አልኖርም ሲቆጨኝ
ቅናት ነው ጠላቴ የሚያነጫንጨኝ
ዳርእስከዳር ብዞር ልክሽን አላገኝ
ልርሳሽ ብል መንፈሴ ሰውም አያረገኝ
እምባዬን ባፈሰው አፍ ላይደቅንበት
የኔ ቃላት ናቸው ፍቅሬን የቀኑበት
አይኔን እየረሳሁ በዛፍ በቅጠሉ
ተብሰልሳይ አርጎኛል ካንቺ መነጠሉ
ትካዜን አጥምደው ምንም ቢፈዙበት
ያዩበታል እንጂ ወፍን አይዙበት
እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ
ተይ አታስጨንቂኝ
እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ
ተይ አታስጨንቂኝ
ልቦናሽ ከኔ አካል ሊርቅ መወሰኑ
ጠፍቶብሽ ይሆን ወይ የመቻል ወሰኑ
አንድም ጸጽቶኛል ለሱም በይኝ ይቅር
አይለመደውም ቅጣት ሰው ሲቀጣው ፍቅር
ልቦናሽ ከኔ አካል ሊርቅ መወሰኑ
ጠፍቶብሽ ይሆን ወይ የመቻል ወሰኑ
አንድም ጸጽቶኛል ለሱም በይኝ ይቅር
አይለመደውም ቅጣት ሰው ሲቀጣው ፍቅር
ኧ.ሀ... ሀ.ሀ... ኧ.ሀ.ሀ.ሀ
ምነው በትዝታ ሁሌ እንደምመኝሽ
ከጉጉቴ መረብ ተቀምጠሸ ባገኝሽ
እኔ አዳኝ አይደለሁ አላልም በጫካ
ምንሽሬ እምባ ነው ህልሜም ባይሳካ
ብዙ ማልቀስ ባዳም ባይለመድ እንኳን
ባንቺ ሀዘን ልቤ ላይ አስጥያለው ድንኳን
ብትባበርኝም ምድር ለአራት ታጥፋ
አብረን እንኑር እና እስኪ አምኜሽ ልጥፋ
ቀራንዮም ይስማ ጎሎጎታም ይወቅ
አይረዳን ምህረቱ እኛ ሳንታረቅ
ባይጻፍም ሰአት ለአለም መጨረሻ
ቀን ማጣት ምጻት ነው አንቺ መመለሻ
እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ
ተይ አታስጨንቂኝ
እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ
ተይ አታስጨንቂኝ
Writer(s): Simone Tsegay
Lyrics powered by www.musixmatch.com