Lyrics

አንድም ቀን ክፉ ቃል ካፏ የማይወጣ ቅሬታን የማታውቅ ካንደበቷ ቁጣ ግድ ነው ግድ ይላል እኔ እሷን ብወድ ሰላሜ ሰላሜ ናት በኔ ማን ሊፈርድ ሰው በጠፋ ጊዜ ሰው ሆና ተገኝታ በልቤ ተርፋለች ደሞ በአይኔ ሞልታ ለምኛት ለመውሰድ እውነትን ተግቼ ዛሬ ብኖር በሷ ሰላሜን አግኝቼ ሰላም የምትሰጥ በመውደድ አስራ ነፍሴን ከነፍሷ ነፍሴን ከነፍሷ አይሆንልኝም ለአንድ ቀን እንኳን ለመራቅ ከሷ ለመራቅ ከሷ አይሆንልኝ እኔስ አይሆንልኝ አንድም ቀን ክፉ ቃል ካፏ የማይወጣ ቅሬታን የማታውቅ ካንደበቷ ቁጣ ግድ ነው ግድ ይላል እኔ እሷን ብወድ ሰላሜ ሰላሜ ናት በኔ ማን ሊፈርድ የደስታ ዘመኔ ከሷ ጋር መጣና ይኧው ሙሉ አረገኝ እድሌም ተቃና በሷ ላይ ያቆመው የልቤ ፍለጋ አብሬያት ዋልኩና ውስጤም ተረጋጋ ሰላም የምትሰጥ በመውደድ አስራ ነፍሴን ከነፍሷ ነፍሴን ከነፍሷ አይሆንልኝም ለአንድ ቀን እንኳን ለመራቅ ከሷ ለመራቅ ከሷ አይሆንልኝ እኔስ አይሆንልኝ
Writer(s): Elias Woldemariam, Meselle Getahun Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out