Top Songs By Madingo Afework
Similar Songs
Credits
AUSFÜHRENDE KÜNSTLER:INNEN
Habesha Music
Künstler:in
Madingo Afework
Künstler:in
KOMPOSITION UND LIEDTEXT
Habesha Music
Songwriter:in
Yilma G/Ab
Songwriter:in
Elias Woldemariam
Songwriter:in
Lyrics
ምነው ለኛ ዳኛ ሸንጎ የለም ባገር
ሸንጎ የለም ባገር
እንደው ለኛ ዳኛ ሸንጎ የለም ባገር
ሸንጎ የለም ባገር
ሲጫን መሄጃሽ ሰረገላ
አዳክመሽዋል የኔን ገላ
በአዋጅ ይነገር ሰው ይጠራ
ይፋ ይወጣል ያንቺም ስራ
ምነው ለኛ ዳኛ ሸንጎ የለም ባገር
ሸንጎ የለም ባገር
እንደው ለኛ ዳኛ ሸንጎ የለም ባገር
ሸንጎ የለም ባገር
ጠዋት ተጫውተን ሳጣሽ ማታ
ባሳብ አደርኩኝ በትዝታ
ጨዋ አንቺ ካለሽ ባገሩ ላይ
አጣፍጪው ፍቅርን ከዚም በላይ
ዘመናይ እቅፍም አልልሽ
ዘመናይ ልልበስሽ ሌት ተቀን
ዘመናይ ብርዱ እንዴት ይውጣልኝ
ዘመናይ እንዲህ ተራርቀን
ዘመናይ ዳኛው ተሰይሞ
ዘመናይ ባስቻለበት ቦታ
ዘመናይ አገኝሽ ይሆን ወይ
ዘመናይ ባቀርብ አቤቱታ
ፍርድ አይወድም እንዴት ይባላል ሰው
ለዚህ አይደል ወይ ካባስ የለበሰው
ባዳባባይ ሀገሩን ሲዳኘው
ህጉ አይደል ወይ ወቶ ያልተገኘው
ያፍቃሪ ጡር እንዲታወቅለት
ለመካሻው እንዲረቀቅለት
በነጋሪት ይውጣለት አዋጅ
ፍትህ አጥቶ እንዳይቀር ወዳጅ
አልጋው ጭር አለ ክፍሉ ቀዝቅዞት
እሱም እንደኔ ትካዜ ገብቶት
ተበደልኩኝ ብል ምን አመጣለው
በምን ከስሼ አስቀጣሻለው
አልጋው ጭር አለ ክፍሉ ቀዝቅዞት
እሱም እንደኔ ትካዜ ገብቶት
ተበደልኩኝ ብል ምን አመጣለው
በምን ከስሼ አስቀጣሻለው
ምነው ለኛ ዳኛ ሸንጎ የለም ባገር
ሸንጎ የለም ባገር
እንደው ለኛ ዳኛ ሸንጎ የለም ባገር
ሸንጎ የለም ባገር
ሲጫን መሄጃሽ ሰረገላ
አዳክመሽዋል የኔን ገላ
በአዋጅ ይነገር ሰው ይጠራ
ይፋ ይወጣል ያንቺም ስራ
ዘመናይ ሹም አለምንብሽ
ዘመናይ አንጥፌው ኩታዬን
ዘመናይ በምን ልገላገል
ዘመናይ ይሄን ትዝታዬን
ዘመናይ ናፍቄሽ ስጎዳ
ዘመናይ ፍቅርሽ ትዝ እያለኝ
ዘመናይ አቤትም ብልብሽ
ዘመናይ ባንቺ ፍትህ የለኝ
ዘውትር ካይኔ ካጠገቤ ሳጣሽ
በምን ዳኛ ጠይቄ ላስቀጣሽ
ልቤ በሀሳብ ችሎት ይደር እንጂ
በፍቅር ላይ የታለ
ካስጠየቀሽ የኔማ ትካዜ
በህልሜ ነሽ ተዳኘሽ ጊዜ
ይግባኝ ብትይ መች ይቀበልሻል
ይሄ ሳይጎልበት መች እሺ ይልሻል
ብከራከርሽ ይዜ ጠበቃ
በፍቅር ጉዳይ ለድል አልበቃ
ስንስማማ እንጂ የእኛ ደስታችን
አንጠቀምም በሙግታችን
ስትከተዪው የራቅሽን እውነት
አዳክመሽዋል የኔን ሰውነት
በመተው መብትሽ ስትጠቀሚ
ርቀሽ እየሄድሽ መስሎሽ ጠቃሚ
Writer(s): Elias Woldemariam, Yilma G/ab
Lyrics powered by www.musixmatch.com