Similar Songs
Credits
AUSFÜHRENDE KÜNSTLER:INNEN
Mastewal Eyayu
Künstler:in
KOMPOSITION UND LIEDTEXT
Mastewal Eyayu
Songwriter:in
Frezer Abebe Werq
Texte
Bruck Afework
Arrangeur:in
Lyrics
አልምልም አልምልም እማ ትሙት ብዬ
ይቅር ባልታመን ቀልድ የለም በእምዬ
እውነቴ አንሳ ለሰው ደርሶ ባይምኑኝ
በምወድሽ ባንቺ እስኪ ማል አሉኝ
ይቅር እምቢ ባያምኑኝ ከምትሞቺብኝ
እኔ አልምልም ትሙት ብዬ ኑሪልኝ እምዬ
እንደ አቦጊዳሄው ከልጅነት ለዛ
ሞትሽ እንደዘበት ከአፍ አድጎ እንደዋዛ
ውለታን ገፍቶ ልጅ በአንደበቱ
ምሎ ይመኛል ሞትን ለእናቱ
ብወድሽም እምቢ ለመታመን በአፌ
አልሰጥም ስምሽን ለሞት አሳልፌ
ገና ለገና ልታመን ብዬ
አልጠራም ስሟን ትሙትስ ብዬ
ገና ለገና ልታመን ብዬ
አልጠራም ስሟን ትሙትስ ብዬ
አልምልም እኔ አልምልም ይቅር
ለዋልሽልኝ ለሰጠሽኝ ፍቅር
ህያው ያርግሽ አይንካብኝ አፈር
ሞት ይርሳልኝ አይንካብኝ አፈር
አልምልም አልምልም እማ ትሙት ብዬ
ይቅር ባልታመን ቀልድ የለም በእምዬ
እውነቴ አንሳ ለሰው ደርሶ ባይምኑኝ
በምወድሽ ባንቺ እስኪ ማል አሉኝ
ይቅር እምቢ ባያምኑኝ ከምትሞቺብኝ
እኔ አልምልም ትሙት ብዬ ኑሪልኝ እምዬ
ከሰው ለመኖር ሲል ለመታመን ብሎ
እንዴድ ይምላል ሰው አንድ እናቱን ገድሎ
ገና ለገና ልታመን ብዬ
አልጠራም ስሟን ትሙትስ ብዬ
ሲሰዋት ለሌላ ሲጨክን የአብራኳ
ትሂድ አጎንብሳ አላት ተረት እንኳ
ላበደርሽኝ ወርቅ እስካለሁ ቆሜ
እኔ አልሰጥሽም ጠጠር ለቅሜ
ላበደርሽኝ ወርቅ እስካለሁ ቆሜ
እኔ አልሰጥሽም ጠጠር ለቅሜ
አልምልም እኔ አልምልም ይቅር
ለዋልሽልኝ ለሰጠሽኝ ፍቅር
ህያው ያርግሽ አይንካብኝ አፈር
ሞት ይርሳልኝ አይንካብኝ አፈር
ህያው ያርግሽ አይንካብኝ አፈር
ሞት ይርሳልኝ አይንካብኝ አፈር
ህያው ያርግሽ አይንካብኝ አፈር
Lyrics powered by www.musixmatch.com