Top Songs By Girma Tefera Kassa
Similar Songs
Lyrics
በመልክሽ አይደል ወይ በቁንጅናሽ
የተረታው ልቤ ከብዶት ዝናሽ
ልሽሽ አልኩኝ ሳይሽ ከምቸገር
ልኑር ርቄ ካንቺ ግን የት ሀገር
ግን የት ሀገር ግን የት ሀገር
በመልክሽ አይደል ወይ በቁንጅናሽ
የተረታው ልቤ ከብዶት ዝናሽ
ልሽሽ አልኩኝ ሳይሽ ከምቸገር
ልኑር ርቄ ካንቺ ግን የት ሀገር
ግን የት ሀገር ግን የት ሀገር
ግን የት ሀገር ግን የት ሀገር
አሳሳቅሽ ያምራል እዳልጠላው
በእኔው መቀለድሽ ሆዴን በላው
ልቤ ሲራራልሽ ማን አመነው
ምን ላርግ ሁለ መናሽ አሳዛኝ ነው
አኳኻንሽ ከሀሳብ መች ይፋቃል
ጥርስሽ አስከፍቶም ይናፈቃል
እየተሳቀብኝ አፈቅራለሁ
ደፍሬ እንዳልነግራት እፈራለው
ምን ነካህ አትፍራ ንገራት
ሂድ ጠጋ በል ጎኗ ተው አውራት
ለሁሉም ጥያቄ መልስ አለው
በይሉኝታ ታጥረህ አትበል እፈራለሁ
ምን ነካህ አትፍራ ንገራት
ሂድ ጠጋ በል ጎኗ ተው አውራት
ለሁሉም ጥያቄ መልስ አለው
በይሉኝታ ታጥረህ አትበል እፈራለሁ
አለሁ ለማለቱ እንዲህ የዘገየሽ
እኔን ማሳበዱ ይሆን ወይ የታየሽ
ልራቅ ከቁንጅናሽ ከሀሳብ ቢነጥለኝ
ቆሜ አላይም ጨርቄን እስኪያስጥለኝ
ምን ነካህ አትፍራ ንገራት
ሂድ ጠጋ በል ጎኗ ተው አውራት
ለሁሉም ጥያቄ መልስ አለው
በይሉኝታ ታጥረህ አትበል እፈራለሁ
በመልክሽ አይደል ወይ በቁንጅናሽ
የተረታው ልቤ ከብዶት ዝናሽ
ልሽሽ አልኩኝ ሳይሽ ከምቸገር
ልኑር ርቄ ካንቺ ግን የት ሀገር
ግን የት ሀገር ግን የት ሀገር
ግን የት ሀገር ግን የት ሀገር
አጥቻለሁ መግቢያ ለመሸሻ
ምንም ስፍራ አይኖርም አንቺን መርሻ
መራቅ እንደማልችል አምኛለው
ዞሬ ዞሬ ካንቺው እገኛለው
አፋልጌ ሳገኝ ደህና መላ
ስወስን ይባባል የኔ ገላ
አለው ስሰናዳ የሚያሳሳ
የት ሄጄ ነው ፍቅሬን የምረሳ
ምን ነካህ አትፍራ ንገራት
ሂድ ጠጋ በል ጎኗ ተው አውራት
ለሁሉም ጥያቄ መልስ አለው
በይሉኝታ ታጥረህ አትበል እፈራልሁ
ምን ነካህ አትፍራ ንገራት
ሂድ ጠጋ በል ጎኗ ተው አውራት
ለሁሉም ጥያቄ መልስ አለው
በይሉኝታ ታጥረህ አትበል እፈራለሁ
አለሁ ለማለቱ እንዲህ የዘገየሽ
እኔን ማሳበዱ ይሆን ወይ የታየሽ
ልራቅ ከቁንጅናሽ ከሀሳብ ቢነጥለኝ
ቆሜ አላይም ጨርቄን እስኪያስጥለኝ
ምን ነካህ አትፍራ ንገራት
ሂድ ጠጋ በል ጎኗ ተው አውራት
ለሁሉም ጥያቄ መልስ አለው
በይሉኝታ ታጥረህ አትበል እፈራለሁ
ምን ነካህ አትፍራ ንገራት
ሂድ ጠጋ በል ጎኗ ተው አውራት
ለሁሉም ጥያቄ መልስ አለው
በይሉኝታ ታጥረህ አትበል እፈራለሁ
Lyrics powered by www.musixmatch.com