Lyrics

ቀና ልብ እስኪቢዲብዳብዴ ካሥማሠ ዮሐና ጤና ይስጥልኝ ነግቷል ፀሐይ ለሁሉ ወጥቷል እይ ወደፊት ወደፊት ቀን ሌላ አዲስ መቷል ማደጊያ ዕድል ሰቷል ሂድ ወደፊት ወደፊት መልስ አይሆን ለድክመትህ ምን ቢበዛ ምክንያትህ ላያስቆም ከውድቀትህ አስጥሎ ካልነገርከው ጉልበትህ አያደርስ ከመርካትህ ቆሞ ፈቅ ማለትን ከልክሎ መች ጠፋና በእውነቱ እንደ አቅምና እንደ እውቀቱ ፈተናው በየቤቱ ታድሎ ዕድል ነው ከማለትህ ከሰነፍ ማብራራትህ ጎልቶ ይታያል ድክመትህ አይሎ ግን እውነትህ ታስሮ ከእምነትህ አትቆጥብ ከምኞትህ ስኬት ነው እንደ ልኬትህ ጣር ሞክር ይበራል አዎ እድገትህ ታስሮ ከእምነትህ አትቆጥብ ከምኞትህ ስኬት ነው እንደ ልኬትህ ተጓዝ መች ይቀራል አዎ የጣረም ይጠራል በል በርታ በርታ በርታ በል ወንድም በርታ በርታ አይዞህ እንዳትረታ በርታ በርታ በርታ በል ወንድም በርታ በርታ አይዞህ እንዳትረታ በርቺ በሏት ጥራት ነሽ ጥቁር ቀይ ዕንቁ ጥሯት ጥራት ነሽ ጥቁር ቀይ ዕንቁ በርቺ በሏት ጥራት ነሽ ጥቁር ቀይ ዕንቁ ጥሯት ጥራት ነሽ ጥቁር ቀይ ዕንቁ (ካሥማሠ) በርታ በይ ልንገርሽ ነገን ላንቺ (ላንቺ) መልክ የንግሥቲቷም ውበት ያንቺ (ያንቺ) እኛ ትናንት መስታወት ባየን ባንቺ (ባንቺ) ሆነሽ አንቺም እንደሷ ባየን አንቺን (አንቺን) ውብ ዓለም እንድትሆን የኛ ዓለም በርቺ (በርቺ) አንድ መላ ነሽ የኛ አንቺ በርቺ (በርቺ) ውብ ዓለም እንድትሆን የኛ አንቺ በርቺ (በርቺ) አንድ መላ ነሽ የኛ ዓለም አንቺ (አንቺ) ቀመር ለኛ ውሎ ደህና ብታበጅ ላንቺ እንጂ ትላንትም ነገም ላንቺ የኛ አለም አንደኛ ነች ሁሌም አዲስ ካንቺ እንጂ ምንኖር ዘውትር መካስ ቆንጅት እውነትሽ ነው ከልብ እምነትሽ ይታይ በዕውቀትሽ እመቤትነትሽ አይቆጠብ ምኞትሽ ስኬት ነው እንደልኬትሽ ለኔ ያልሽው ይበራል እኅት ጥልቀትሽ ሲዘል ከውበትሽ ያነቃል ህይወትሽ ክብርሽ ሴትነትሽ አይቆጠብ ምኞትሽ ስኬት ነው እንደልኬትሽ መድረስ መች ይቀራል አዎ የጣረም ይጠራል በይ በርቺ በርቺ በርቺ የኛ እኅት በርቺ በርቺ አይዞሽ እንዳትረቺ በርቺ በርቺ በርቺ እኅቴም ጠንክሪ አንቺ አይዞሽ እንዳትረቺ በርቺ በሏት ወንድም እሱም ይበርታ ጥሯት እኅት ዓለም ትበርታ በርቺ በሏት ወገን ሁሉም ይበርታ ጥሯት ነገም ይመርባታ በርታ በይ ልንገርሽ ነገን ላንቺ (ላንቺ) መልክ የንግሥቲቷም ውበት ያንቺ (ያንቺ) እኛ ትናንት መስታወት ባየን ባንቺ (ባንቺ) ሆነሽ አንቺም እንደሷ ባየን አንቺን (አንቺን) በርታ አንተም በርታ በርቺ አንቺም በርቺ በርታ አንተም በርታ በርቺ አንቺም በርቺ በርታ አንተም በርታ በርቺ አንቺም በርቺ በርታ አንተም በርታ በርቺ አንቺም በርቺ በርታ አንተም በርታ በርቺ አንቺም በርቺ
Writer(s): Unknown Unknown, Samuel Alemu Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out