Lyrics

መች አወኩት የሷን ሁኔታ በልቧ ውስጥ ያለኝን ቦታ ወይ ቀርቢያት እንዳልረዳ እንቆቅልሽ ሆና ተጎዳ ትውደደኝም ወይ አትውደደኝ የልቧን ምት ማወቅ ከበደኝ ስትፈልገኝ አለው ብላት ስፈልጋት አላገኛት ግድ ያላልሽው የኔን ጉዳይ የትም አይሄድ ብለሽ ነው ወይ የትም አይሄድ ያሉት ናቅ አርገው የሄደ ቀን ትርፉ ፀፀት ነው ዋጋው ሲያልቅ ያበዙት ቸልታ አንዲቷ የፍቅር ጠብታ ያስርባል ያስጠማል ካለፈ ከገፋ አይፀድቅም ወይ ያቀፈ ግድ የለሽም ቃሌን ስሚው ባይጥምሽም -ግድ የለሽም ይጠቅምሻል አይጎዳሽም -ግድ የለሽም አወዛውዞ ባይጥልሽም -ግድ የለሽም ጅል ነው ፍቅር አይለቅሽም ግድ የለም 3× ይሁን ግድ አይደለም ትግስቴን ጨርሼ ፊቴን እስካዞረው ወይ አንቺን አግብቼ ህልሜን አስክኖረው አልተውሽም የትም በዋዛ ነገር እልህ ያስጨርሳል መቼም ያንቺ ነገር ግድ የለሽም ቃሌን ስሚው ባይጥምሽም -ግድ የለሽም ይጠቅምሻል አይጎዳሽም -ግድ የለሽም አወዛውዞ ባይጥልሽም -ግድ የለሽም ጅል ነው ፍቅር አይለቅሽም ፍልስፍና ወይ ሳይኮሎጂ ትምህርት አይደል ፍቅር ነው እንጂ እንዳጠምደው ልቧን በዘዴ ስልት ስማር ልኖር ነው እንዴ ትውደደኝም ወይ አትውደደኝ የልቧን ምት ማወቅ ከበደኝ ስትፈልገኝ አለው ብላት ስፈልጋት አላገኛት ደሞ ደስ ሲላት አንዳንዴ አለሁህ ትላለች በዘዴ አንድዳ ለማብረድ ተፈጥራ አልገባህም አለኝ ነገሯ ግድ የለሽም ቃሌን ስሚው ባይጥምሽም -ግድ የለሽም ይጠቅምሻል አይጎዳሽም -ግድ የለሽም አወዛውዞ ባይጥልሽም -ግድ የለሽም ጅል ነው ፍቅር አይለቅሽም ግድ የለም 3× ይሁን ግድ አይደለም ከውጣውረዱ ካየሁት በዚ አለም እንዳንቺ ፈተና የከበደኝ የለም ቀለል አረጊው ይሄን ቀለል አርጊው በቃ ከመሸ አይደገም እድሜ እንደ ሙዚቃ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out