Similar Songs
Credits
AUSFÜHRENDE KÜNSTLER:INNEN
Bisrat Garedew
Künstler:in
KOMPOSITION UND LIEDTEXT
Bisrat Garedew
Songwriter:in
Lyrics
ተጋሪም የለሽም አትስጊ አታስቢ
ግዛትሽ ነው ቅጥሩ ላንቺ የልቤ ግቢ
ተጋሪም የለሽም አትስጊ አታስቢ
ግዛትሽ ነው ቅጥሩ ላንቺ የልቤ ግቢ
ያፀደቅሻት ነፍሴን ተስፋ አጥታ ጠውልጋ (ጠውልጋ)
ነፍስ የዘራሽባት አንችው ነሽ የሰጠሻት ዋጋ
እዘዥበት ልቤን ቅጥሩም ግዛትሽ ነው የግልሽ (የግልሽ)
ሌላ ምንም የለም ይሄ ይመጥንሻል የምልሽ
ሎሌም ሆናለች በውዴታ
ስላወጣሻት ከሁካታ
ሰላምሽንም ሌት በፀሎቷ
ነፍሴ አድራለች ተቀኝታ
ተጋሪም የለሽም አትስጊ አታስቢ
ግዛትሽ ነው ቅጥሩ ላንቺ የልቤ ግቢ
ተጋሪም የለሽም አትስጊ አታስቢ
ግዛትሽ ነው ቅጥሩ ላንቺ የልቤ ግቢ
የመሸጋገሪያ እርካብም የሆንሻት (የሆንሻት)
አንቺው ነሽ መክሊቷ ለዚህ ያበቃሻት ያየሻት
ትኖሪያለሽ ውስጤ ሁሌም ትልቅ ቦታ ይዘሽ (ይዘሽ)
ገላዬም የግልሽ ያንቺው እንደሆነ የብቻሽ
ሎሌም ሆናለች በውዴታ
ስላወጣሻት ከሁካታ
ሰላምሽንም ሌት በፀሎቷ
ነፍሴ አድራለች ተቀኝታ
ሰላምሽንም ሌት በፀሎቷ
ነፍሴ አድራለች ተቀኝታ
ሰላምሽንም ሌት በፀሎቷ
ነፍሴ አድራለች ተቀኝታ
Written by: Bisrat Garedew