Lyrics

ከአፈሩ ቆሜ ከማረፊያሽ ላይ
እርፍ እርፍ ሰላም ተኚ
መቼም ጎኔ አትሆኚ
ከላይ ባዘጋጀዉ በሱ ተኚ
በገነት ቦታ ደና ሆኚ
ከአፈሩ ቆሜ ከማረፊያሽ ላይ
እርፍ እርፍ ሰላም ተኚ
መቼም ጎኔ አትሆኚ
ከላይ ባዘጋጀዉ በሱ ተኚ
በገነት ቦታ ደና ሆኚ
እህቴ እቴን እቴን እቴን ሲወስዳት እህቴን
ቡጮህስ ለማ ለማ ለማ የሞተ ላይሰማ
አንተዉ ካመጣኸዉ ምን እላለዉ
እኔም በተራዬ እሄዳለዉ
ማን ይቀራልና ከመጣበት
አንተ መልእክተኛ ደርሶበት
እርሜን አወጣለዉ እኔም በቤቴ
ላረፈቺዉ ቆንጆ ለአንዲት እህቴ
ንፁህ አንድ ልጇን እያዩባት
በገበታዬ ላይ እስቲ ላንሳት
አኑረኝ ለልጇ ስማኝ ጌታዬ
መፅናኛ ላክልኝ ይድረቅ እምባዬ
ልጇን ልጄ ብዬ ላሳድጋት
እኔዉ ነኝ ተጠሪ ሰዉም የላት
አኑረኝ ለልጇ ስማኝ ጌታዬ
መፅናኛ ላክልኝ ይድረቅ እምባዬ
ልጇን ልጄ ብዬ ላሳድጋት
እኔዉ ነኝ ተጠሪ ሰዉም የላት
አንተዉ ካመጣኸዉ ምን እላለዉ
እኔም በተራዬ እሄዳለዉ
ማን ይቀራልና ከመጣበት
አንተ መልእክተኛ ደርሶበት
እርሜን አወጣለዉ እኔም በቤቴ
ላረፈቺዉ ቆንጆ ለአንዲት እህቴ
ንፁህ አንድ ልጇን እያዩባት
በገበታዬ ላይ እስቲ ላንሳት
Written by: Abel mulugeta
instagramSharePathic_arrow_out