Lyrics

ወደድኩሃ እኔ ፈለኩሃ
መመኘት መብቴ ነው ምንም አቅሜ ቢያንሰኝ ብሆን ደሃ
ባላውቅም አንተን ላግኝህ ልጣ
መውደድ ጥፋት ሆኖ አልቀጣ
ዝም አልልም ዘውድ አለ በልቤ
አልልም ዙፋን አለው ልቤ
ዝም አልልም ዘውድ አለ በልቤ
አልልም ዙፋን አለው ልቤ
አዝዤ አላሶጣ ነጋሪት ዋይዋይ ነጋሪት እምቢልታ እምቢልታ
ክብሬን አያደምቀው ሀገሬው ዋይዋይ ሀገሬው በእልልታ በእልልታ
ንግስትም አይደለሁ ንጉስም ዋይዋይ ንጉስም አይወልደኝ አይወልደኝ
በድህነቴ ነው ልዑል ዋይዋይ ልኡል ያስወደደኝ ያስወደደኝ
ልዑል አስወደደኝ
ልዑል አስወደደኝ
ልዑል አስወደደኝ
ልዑል አስወደደኝ
ልዑል አስወደደኝ
ልዑል አስወደደኝ
ልዑል አስወደደኝ
ልዑል አስወደደኝ
ልዑል አስወደደኝ
ልዑል አስወደደኝ
ጥፋተኛ ካላረገኝ ዳኛ
እኔስ ፍላጎቴ ከወዳጅ ልዑል ነው ከጤፍ ማኛ
ይህ ልቤ ሁሌ እሩቅ ይመኛል
ዛሬ ምን ንጉስ ቤት ያሰኘኛል
ዝም አልልም ዘውድ አለ በልቤ
አልልም ዙፋን አለው ልቤ
ዝም አልልም ዘውድ አለ በልቤ
አልልም ዙፋን አለው ልቤ
መጥቼ እንዳላይህ ባካልም ዋይዋይ ባካልም በገላ በገላ
ካንተ ምደርስበት እኔ እንደው ዋይዋይ የለኝ ሰረገላ እኔ እንደው
በሞካሹ ጥበብ ሳላጌጥ ዋይዋይ ሳላጌጥ በካባ በካባ
ካንተ ቤተ መንግስት በምኔ ዋይዋይ በምኔ ልገባ ልገባ
በምኔ ልገባ
በምኔ ልገባ
በምኔ ልገባ
በምኔ ልገባ
በምኔ ልገባ
በምኔ ልገባ
በምኔ ልገባ
በምኔ ልገባ
በምኔ ልገባ
በምኔ ልገባ
በምኔ ልገባ
ዙፋንህ ነው ልቤ ዙፋንህ ነው
ዙፋንህ ነው ልቤ ዙፋንህ ነው
Written by: Elias Woldemariam, Yilma G/Ab
instagramSharePathic_arrow_out