Top Songs By Bezuayehu Demissie
Lyrics
ፀጥ ባለው ገጠር ጭር ባለ ቦታ
በአበቦች መካከል ቁጭ ብለን በእርጋታ
እንደዛሬ ሳይሆን ፍቅር በጥላቻ
ተጫውተን ነበረ እኔና አንቺ ብቻ
ጭር ባለ ሌሊት ባ'ልጋ ላይ ተኝተን
ማንም ሰው ሳያየን ሳይመለከተን
ምነው በዚያ ጊዜ አጃቢ በኖረን
ምን ብለሺኝ ነበረ ምን ብዬሽ ነበረ
ፀጥ ባለው ገጠር ጭር ባለ ቦታ
በአበቦች መካከል ቁጭ ብለን በእርጋታ
እንደዛሬ ሳይሆን ፍቅር በጥላቻ
ተጫውተን ነበረ እኔና አንቺ ብቻ
አቅፌሽ አቅፈሽኝ ካፊያ እየጣለብን
ብርድልብስ አንሻም ተኝተን ሲሞቀን
ያለፈውን ፍቅር አስበሽ ገምቺኝ
ማን ነበረ ያለ እኔ ማን ነበረ ያ'ላንቺ
ፀጥ ባለው ገጠር ጭር ባለ ቦታ
በአበቦች መካከል ቁጭ ብለን በእርጋታ
እንደዛሬ ሳይሆን ፍቅር በጥላቻ
ተጫውተን ነበረ እኔና አንቺ ብቻ
እንዴት እንደነበር ያለፈው ፍቅራችን
አንዳንዱን አስታውሺ ስለሁኔታችን
አንነጣጠልም በቃልሽ ብለሺኝ
እንዴት ረሳሁሽ እንዴት ረሳሺኝ
ፀጥ ባለው ገጠር ጭር ባለ ቦታ
በአበቦች መካከል ቁጭ ብለን በእርጋታ
እንደዛሬ ሳይሆን ፍቅር በጥላቻ
ተጫውተን ነበረ እኔና አንቺ ብቻ
Written by: