Top Songs By Bezuayehu Demissie
Credits
AUSFÜHRENDE KÜNSTLER:INNEN
Bezuayehu Demissie
Künstler:in
KOMPOSITION UND LIEDTEXT
Amanuel Yilma
Songwriter:in
Lyrics
በዋልሽበት ቦታ ባለፍሽበት መንደር
ምነው እንደ ጠላት ለኔ የማይነገር
ሰው አለፈች ቢሉኝ ተከትዬሽ ነበር
ባጣሽም ቅር አለኝ ሳላይሽም ስቀር
በዋልሽበት ቦታ ባለፍሽበት መንደር
ምነው እንደ ጠላት ለኔ የማይነገር
እንዴት እንደምሆን ባየሽ ምን ነበር
ጉዳይም የለኝም ካንቺ ሃሳብ በቀር
ቅኔ ቢሉኝ ቤትሽ መኖሪያሽ መገኛው
እኔ ነኝ ዘራፊሽ በሌት የማልተኛው
ሃሳብ ደጅ አውሎኝ አርጎኝ ስደተኛ
ደሞ እንደኔም ካለ ማነው ንገሪኛ
መርሳት እንዳረጉት እንዳቀመሱት ሰው
አለፍሽ ባሉኝ ቁጥር ዱካሽን ሳስሰው
ምን ቢሆን ነው ፍቅርሽ ያየለው ጉልበቱ
አቅሜን እስከማጣ ደቆሰኝ በብርቱ
እንደ ወፍ ሌት በማለዳ
ሊያበረኝ ያንቺ የፍቅር እዳ
መላ ነሽ አንቺ ሰው መላ
ያላንቺ የለም ሰው ሌላ
እንደ ወፍ ሌት በማለዳ
ሊያበረኝ ያንቺ የፍቅር እዳ
መላ ነሽ አንቺ ሰው መላ
ያላንቺ የለም ሰው ሌላ
በዋልሽበት ቦታ ባለፍሽበት መንደር
ምነው እንደ ጠላት ለኔ የማይነገር
ሰው አለፈች ቢሉኝ ተከትዬሽ ነበር
ባጣሽም ቅር አለኝ ሳላይሽም ስቀር
በዋልሽበት ቦታ ባለፍሽበት መንደር
ምነው እንደ ጠላት ለኔ የማይነገር
እንዴት እንደምሆን ባየሽ ምን ነበር
ጉዳይም የለኝም ካንቺ ሃሳብ በቀር
መውደድ ምን አባቱ አልልም ብከፋ
ባንቺው ከመጣብኝ ያለኝስ ቢጠፋ
ትርፍ ሃብት ገንዘቤም ከእንግዲህ በኋላ
ካንቺ ጋር መጓዝ ነው የለኝ ሀሳብ ሌላ
እንኳን ለወደዱት በልብ ለሚቀመጥ
ካለ በምድር ላይ ሰው ያለውን ቢሰጥ
ለፍቅር ቢከፈል ይሄም ያንስበታል
ብዙ ሰው አትርፎ ፍቅር ጎሎበታል
እንደ ወፍ ሌት በማለዳ
ሊያበረኝ ያንቺ የፍቅር እዳ
መላ ነሽ አንቺ ሰው መላ
ያላንቺ የለም ሰው ሌላ
እንደ ወፍ ሌት በማለዳ
ሊያበረኝ ያንቺ የፍቅር እዳ
መላ ነሽ አንቺ ሰው መላ
ያላንቺ የለም ሰው ሌላ
እንደ ወፍ ሌት በማለዳ
ሊያበረኝ ያንቺ የፍቅር እዳ
መላ ነሽ አንቺ ሰው መላ
ያላንቺ የለም ሰው ሌላ
እንደ ወፍ ሌት በማለዳ
Writer(s): Elias Woldemariam, Amanuel Yilma
Lyrics powered by www.musixmatch.com