Credits
AUSFÜHRENDE KÜNSTLER:INNEN
Abenet Agonafer
Künstler:in
KOMPOSITION UND LIEDTEXT
Abenet Agonafer
Songwriter:in
Lyrics
አአ ይቅርብኝ
አአ ይቅርብኝ
አትማይብኝ
አአ ይቅርብኝ
አአ ይቅርብኝ
ሙት አትበይኝ
አአ ይቅርብኝ
አአ ይቅርብኝ
አትማይብኝ
አአ ይቅርብኝ
አአ ይቅርብኝ
ሙት አትበይኝ
ከወለዱሽ አስበልጠሽ
ስሜን ጠርተሽ እንዲያምርብሽ
እያለሁኝ ድረስ ብለሽ
እያራቅሽኝ ነው ከጎንሽ
ናፍቀሽ እምነት የፍቅር ጉርሻ
ስሜ ቀሎሽ ለኣፍ ማሟሻ
ሙት ሙት ብቻ አትበይኝ
ልኑር ለምን አትግደይኝ
ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ
ይግባሽ ትርጉሙ እንድንስማማ
ከልብሽ ሳልኖር ላፍሽ ሞልቼ
ስትገይኝ ኖርኩኝ ለወዳጆቼ
ጨክኜ አልምልም ስምሽን ጠርቼ
እየተላለፍኩ እውነትን ትቼ
አትማይ አትማይ
አትማይ በስሜም በኔ
እንዳላምንሽ ስንቴ
ታዘበሽ አይኔ
አትማይ አትማይ አትማይ በስሜም በኔ
ነብሴን ንቀሽ ስሜን ወደሽው ከኔ
ስትሰርቂ ላመልሽ ያውም ፈቅደሽ ባረግሽው
ምን ይሉት ፈሊጥ ነው ድረስልኝ ምትይው
በክፉ ቀን ጊዜሽ ብትጠሪኝም ወይ ብዬ
እንዳልመጣ አድርጎኛል አውቆብሻል ጆሮዬ
እውነተኛ አፍቃሪ ቢምልም በየሰበቡ
ሳይርቅ ነው አንደበቱን ከልቡ
ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ
ይግባሽ ትርጉሙ እንድንስማማ
ከልብሽ ሳልኖር ላፍሽ ሞልቼ
ስትገይኝ ኖርኩኝ ለወዳጆቼ
ጨክኜ አልምልም ስምሽን
ጠርቼ እየተላለፍኩ እውነትን ትቼ
አትማይ አትማይ አትማይ በስሜም በኔ
እንዳላምንሽ ስንቴ ታዘበሽ አይኔ
አትማይ አትማይ አትማይ በስሜም በኔ
ነብሴን ንቀሽ ስሜን ወደሽው ከኔ
ከወለዱሽ አስበልጠሽ
ስሜን ጠርተሽ እንዲያምርብሽ
እያለሁኝ ድረስ ብለሽ
እያራቅሽኝ ነው ከጎንሽ
የ እምነት የፍቅር ጉርሻ
ስሜ ቀሎሽ ለኣፍ ማሟሻ
ሙት ሙት ብቻ አትበይኝ
ልኑር ለምን አትግደይኝ
ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ
ይግባሽ ትርጉሙ እንድንስማማ
ከልብሽ ሳልኖር ላፍሽ ሞልቼ
ስትገይኝ ኖርኩኝ ለወዳጆቼ
ጨክኜ አልምልም ስምሽን
ጠርቼ እየተላለፍኩ እውነትን ትቼ
አትማይ አትማይ አትማይ በስሜም በኔ
እንዳላምንሽ ስንቴ ታዘበሽ አይኔ
አትማይ አትማይ አትማይ በስሜም በኔ
ነብሴን ንቀሽ ስሜን ወደሽው ከኔ
በቀን ውስጥ አስሬ ለምን ባፍሽ ሞታለሁ
በሆነው ባልሆነው አረ በምን እዳዬ ነው
ይቅር ተይ አትማይ በስሜ በየሰበብሽ
ግድ የለም አይጎዳም እውነት ካልሽ እውነትን ይዘሽ
ስቅ እስኪለው ድረስ ቢነሳም የተወደደ
የጠራው ፍቅር ነው ከነፍሱ የተዋሃደ
ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ይግባሽ ትርጉሙ እንድንስማማ
ከልብሽ ሳልኖር ላፍሽ ሞልቼ ስትገይኝ ኖርኩኝ ለወዳጆቼ
ጨክኜ አልምልም ስምሽን ጠርቼ እየተላለፍኩ እውነትን ትቼ
አትማይ አትማይ አትማይ በስሜም በኔ
እንዳላምንሽ ስንቴ ታዘበሽ አይኔ
አትማይ አትማይ አትማይ በስሜም በኔ
ነብሴን ንቀሽ ስሜን ወደሽው ከኔ
አትማይ አትማይ አትማይ በስሜም በኔ
Lyrics powered by www.musixmatch.com