Credits
AUSFÜHRENDE KÜNSTLER:INNEN
Dawit Tsige
Künstler:in
KOMPOSITION UND LIEDTEXT
Dawit Tsige
Songwriter:in
Lyrics
የኔ ፍቅር የግሌ ነሽ ሳቅ በይ አንዴ ልይሽ
የኔ ፍቅር የግሌ ነሽ ሳቅ በይ አንዴ ልይሽ
የኔው ነሽ የኔ ብቻ አይደለሽም የሌላ
ቃልኪዳን ገባሁልሽ ላልከዳሽ በመሀላ
በእኔ ሰላምሽ ይብዛ ያኩራሽ ላንቺ ማደሬ
አስደስቼሽ ልደሰት አለኝታዬ ነሽ ፍቅሬ
የኔ ፍቅር የግሌ ነሽ ሳቅ በይ አንዴ ልይሽ
የኔ ፍቅር የግሌ ነሽ ሳቅ በይ አንዴ ልይሽ
የፍቅር ማጣፈጫ ቅመም አለው ጨዋታሽ
ሳቅ ስትይ ካላየሁ አልደምቅም በዝምታሽ
አጥቼስ ውዬ ሳድር አይረጋልኝም ልቤ
ጭር እላላሁ ያላንቺ አትራቂ ካጠገቤ
የኔ ፍቅር የግሌ ነሽ ሳቅ በይ አንዴ ልይሽ
የኔ ፍቅር የግሌ ነሽ ሳቅ በይ አንዴ ልይሽ
ኮከባችን ገጥሞልን አጣምሮን እጣ ፋንታ
ስሜትን ያጋራናል ፍቅራችን እንደመንታ
ከታመምሽም መታመም ደስ ሲልሽ ደስታዬ
የሆንሽውን ለመሆን ልብሽ ላይ ነው ቦታዬ
የኔ ፍቅር የግሌ ነሽ ሳቅ በይ አንዴ ልይሽ
የኔ ፍቅር የግሌ ነሽ ሳቅ በይ አንዴ ልይሽ
Lyrics powered by www.musixmatch.com