Similar Songs
Credits
KOMPOSITION UND LIEDTEXT
Michael Belayneh
Songwriter:in
Solomon Sahele
Songwriter:in
PRODUKTION UND TECHNIK
Michael Belayneh
Produzent:in
Kirubel Tesfaye
Mischtechniker:in
Melaku Sisay
Produzent:in
Lyrics
የመዋደድ ኬላ የፍቅር ድንበሩ
መናፈቅ እኮ ነው የፍቅር ደምሥሩ
አለሽ ጨረቃ ላይ አለሽ ከሰማዩ
የትም አይሻለሁ የኔ ክፋይ ሙሉ
የጤዛላይ ዉሃ እንክብል ጠበታ
ከነፋስ ያዋለ ሰንበሌጥ ሹክሹክታ
ካንደኛዉ ትንፋሼ አንደኛዉ ሲቀጠል
አንቺን ነዉ የማስብ ቀፅበቱ መሀል
ገና በማለዳው ንጋት ሲንጠራራ
አውራ ዶሮ ጮኾ ፀሐይዋን ሲጣራ
ለኔ ብለሽ ስሚ ላንቺ ነው መልዕክቱ
ልቤ ይወድሻል ይኼ ነው እውነቱ
በልከኛ ሚዛን ፍቅርን አክባሪ
በለምለም ሰንበሌጥ ቃልኪዳን አሳሪ
ለክ እንደ ዳክዬ ደግሞ እንደ ዋኔ
ዙሪያሽን የምከብ ለመምቴሽ ነኝ እኔ
ገና በማለዳው ንጋት ሲንጠራራ
አውራ ዶሮ ጮኾ ፀሐይዋን ሲጣራ
ለኔ ብለሽ ስሚ ላንቺ ነው መልዕክቱ
ልቤ ይወድሻል ይኼ ነው እውነቱ
ካንደኛው ትንፋሼ ሌላኛውን ስስብ
በቅጽበቱ መኻል አንቺን ነው የማስብ
የትም ቦታ ኾኜ የትም ቦታ ኾነሽ
እናፍቅሻለሁ ትናፍቂኛለሽ
ገና በማለዳው ንጋት ሲንጠራራ
አውራ ዶሮ ጮኾ ፀሐይዋን ሲጣራ
ለኔ ብለሽ ስሚ ላንቺ ነው መልዕክቱ
ልቤ ይወድሻል ይኼ ነው እውነቱ
በታላቅ አርምሞ በተገኘ ዜማ
ንጋት ልታበስር ከጮራዋ ቀድማ
ጸሎት ማድረሻ ላይ በሌሊቱ ቆማ
ኩኩ መለኮቴ ስትዘምር ደጋግማ
ለኔ ብለሽ ስሚ ላንቺ ነው መልዕክቱ
ልቤ ይወድሻል ይኼ ነው እውነቱ
ገና በማለዳው ንጋት ሲንጠራራ
አውራ ዶሮ ጮኾ ፀሐይዋን ሲጣራ
ለኔ ብለሽ ስሚ ላንቺ ነው መልዕክቱ
ልቤ ይወድሻል ይኼ ነው እውነቱ
Written by: Michael Belayneh, Solomon Sahele