Top Songs By Aregahegn Worash
Credits
AUSFÜHRENDE KÜNSTLER:INNEN
Aregahegn Worash
Künstler:in
KOMPOSITION UND LIEDTEXT
Aregahegn Worash
Songwriter:in
Lyrics
እንዴት አረግሽው?
የእምነቴን ኪዳን ቃል
ትቼሽ እኖራለሁ በቃ
በቃ በቃ
ከንግዲህ ሁሉም ይብቃ
እንዴህ ካረግሽው
የእምነቴን ኪዳን ቃል
ትቼሽ እኖራለሁ በቃ
በቃ በቃ
ከንግዲህ ሁሉም ይብቃ
መዋደዴ መቼ ረዳኝ
ሰዉ ሲጎዳኝ ፣ ሰው ሲከዳኝ
መላ አጥቼ በዛ ሀዘኔ
ምነው ቢቀር መባዘኔ
በራሴ ሀሳብ አርጎኝ መናኝ
አጣው ወዳጅ የሚያፅናናኝ
መች ሲታወቅ ሆዴ የገባ
ሰው የሚያየው ያይኔን እምባ
እርም በል ሆዴ ተው ይብቃ
እንዴት አረግሽው?
የእምነቴን ኪዳን ቃል
ትቼሽ እኖራለሁ በቃ
በቃ በቃ
ከንግዲህ ሁሉም ይብቃ
እንዴህ ካረግሽው?
የእምነቴን ኪዳን ቃል
ትቼሽ እኖራለሁ በቃ
በቃ በቃ
ከንግዲህ ሁሉም ይብቃ
ሆኖ እድሌ እሾህ አብቃይ
እያስወጋኝ ከምሰቃይ
መብሰልሰሌን ትቶት ልቤ
ሰብሰብ ይበል ባዛኝ ቀልቤ
ስራሽ ውስጤን አርጎት ጨካኝ
ሰው መበቀል ባያረካኝ
ምን አጥፍቼ ምን አጉድዬ
ልኑር ዘውትር ተበድዬ
እርም በል ሆዴ ተው ይብቃ
Writer(s): Aregahegn Worash, Elias Melka
Lyrics powered by www.musixmatch.com