Top Songs By Zemari Deacon Abel Mekbib
Similar Songs
Credits
AUSFÜHRENDE KÜNSTLER:INNEN
Zemari Deacon Abel Mekbib
Künstler:in
KOMPOSITION UND LIEDTEXT
Mekuria Gugsa
Songwriter:in
Lyrics
ምልክቴ ነሽ ድንግል ለህይወቴ
ባንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ
ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ
ጸጋሽ ጎብኝቶኝ ቃልኪዳንሽ
ምልክቴ ነሽ ድንግል ለህይወቴ
ባንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ
ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ
ጸጋሽ ጎብኝቶኝ ቃልኪዳንሽ
ተስፋ ያርኩት አልተበተነም
እንባዬ ማሬት ከቶ አልወደቀም
ለበጎ ሆነ ማልቀስ ማንባቴ
ሰላም ሰፈነ በእልፍኝ በቤቴ
ቅኔ ነጠኩኝ ያባ ጊዮርጊስን
ቆምኩኝ ቅዳሴ የሕርያቆስን
የያሬድ ዜማ ሞላ በልቤ
የለም ወጀቡ ቀርባኝ መርከቤ
ምልክቴ ነሽ ድንግል ለህይወቴ
ባንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ
ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ
ጸጋሽ ጎብኝቶኝ ቃልኪዳንሽ
ወገቤን ታጠኩ ጭንቀቴን ጥዬ
ዛሬስ በድስታ ይፍሰስ እንባዬ
የኃዘን ልብሴን ድንግል ቀይራ
የደበዘዘው ሕይወቴ በራ
አራራይ ዜማ ዛሬ ተማርኩኝ
ፍቅሯ አሽነፈኝ እጄን ሰጠሁኝ
ቅኔ በልቤ ተመላለሰ
የድንግል ክብር ዉስጤ ነገሰ
ምልክቴ ነሽ ድንግል ለህይወቴ
ባንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ
ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ
ጸጋሽ ጎብኝቶኝ ቃልኪዳንሽ
የዘረጋሁት እጄ ተሞላ
ማርያም ሆናልኝ ጥላ ከለላ
የዉስጤ ፀሎት ዛሬ ሌላ ነው
የድንግል ክብር ምልጃው ቀየረው
ዛሬ ጎጆዬ አንፀባረቀች
ያማረ ሰንፔር እንቁ መሰለች
ቀንዴ ከፍ ከፍ አለልኝና
ሰዋሁ ለድንግል ይህን ምስጋና
ምልክቴ ነሽ ድንግል ለህይወቴ
ባንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ
ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ
ጸጋሽ ጎብኝቶኝ ቃልኪዳንሽ
ምልክቴ ነሽ ድንግል ለህይወቴ
ባንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ
ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ
ጸጋሽ ጎብኝቶኝ ቃልኪዳንሽ
Written by: Mekuria Gugsa