Lyrics

ቀራንዮ ቀራንዮ ጐለጐታ
ባንቺ ምድር ያለም ጌታ
ተጨነቀ ተሰቃየ ተንገላታ
በማይቀለ ምድር ዙፋን መስቀል ተክሎ
ልብስን አለበሰን እርቃኑን ተሰቅሎ
ስራችን ተሻረ በመከራ ቆስሎ
ቁስላችን ተሻረ በመከራ ቆስሎ
ያማረ ልብስ የለው ደም ሆኗል ቀሚሱ
የወርቅ ካባ የለው እርቃኑን ነው እሱ
በፍቅር ይገዛል ተሰቅሎ ንጉሱ
ቀራንዮ ቀራንዮ ጐለጐታ
ባንቺ ምድር ያለም ጌታ
ተጨነቀ ተሰቃየ ተንገላታ
የስልጣኑ በትር በእጁ የያዘው
ሳዶር እና ናዶር የበትር ሚስማር ነው
እየቸነከሩት አላማው ፍቅር ነው
ሞታችንን ወስዶ ሂወቱን ሸለመ
ህሙማንን ሊያድን ለፍቅር ታመመ
ከውድቀት ሊያነሳን ወደቀ ደከመ
ቀራንዮ ቀራንዮ ጐለጐታ
ባንቺ ምድር ያለም ጌታ
ተጨነቀ ተሰቃየ ተንገላታ
ስለኛ ብለህ ተንገላታህ
Written by: Abel Mekbib
instagramSharePathic_arrow_out