Music Video

Featured In

Credits

AUSFÜHRENDE KÜNSTLER:INNEN
Tsehay Yohannes
Tsehay Yohannes
Künstler:in
KOMPOSITION UND LIEDTEXT
Tsehay Yohannes
Tsehay Yohannes
Songwriter:in

Lyrics

ቅያሜ እንኳን ቢኖር ቢበዛም ባይበዛም
ሚስጥርን ያወያዩት ወዳጅ አይረሳም
ለመልካም ፍቅረኛ እንደደግነቱ
ፈገግታም ቁርስ ነው ጠብ ይላል ከአንጀቱ
ፊትሽን ወደኔ መለስ
ዓይኔን በዓይንሽ አሰስ
በአለንጋ ጣትሽ ዳበስ
ገላዬን አርጊው ዳሰስ
ፍቅር በኛ ላይ ይንገስ
ያኔ
ፈካ ፤ ነቃ ፤ ጎርደድ ፤ ፈንደቅ ፤ ደመቅ
ያንተው ነኝ በይኝ
ከጎነሽ አርጊኝ
ያገርሽ ልጅ ነኝ
ያንተው ነኝ በይኝ
ከጎነሽ አርጊኝ
ያገርሽ ልጅ ነኝ
የኔ ከልቤ ላይ አልተፋቀልኝም
ሳይሽ ይጨንቀኛል አልቆረጠልኝም
በቃ ልርሳው ብዬ ለመተው ስወስን
የፍቅርሽ ትዝታ እየመጣ ድቅን
ናፍቄ ሳይሽ ክርትት
ዓይኔ ከዓይንሽ ላይ ቅርት
ምን ነካህ በይኝ ቀርበሽ
ባለንጋ ጣትሽ ዳብሰሽ
ፍቅር በኛ ላይ ይንገስ
ያኔ
ቀረብ ፤ ሰብሰብ፤ ለመድ ፤ ወደድ ፤ ጎርደድ
ያንተው ነኝ በይኝ ፤ ያንተው ነኝ በይኝ
ከጎንሽ አርጊኝ
ያንተው ነኝ በይኝ
ከጎንሽ አርጊኝ
ያገርሽ ልጅ ነኝ
እምባ ይገዳል ወይ ካንጀት ካለቀሱ
ለፍቅር ተስማሚ ማር ነው ከንፈርመሱ
ወዶ የባዘነ ናፍቆት የነካካው
ያሰበው ካልሆነ የለም የሚያረካው
ፊትሽን ወደኔ መለስ
ዓይኔን በዓይንሽ አሰስ
በአለንጋ ጣትሽ ዳበስ
ገላዬን አርጊው ዳሰስ
ፍቅር በኛ ላይ ይንገስ
ያኔ
ፈካ ፤ ነቃ ፤ ጎርደድ ፤ ፈንደቅ ፤ ደመቅ
ያንተው ነኝ በይኝ
ከጎነሽ አርጊኝ
ያገርሽ ልጅ ነኝ
ያንተው ነኝ በይኝ
ከጎነሽ አርጊኝ
ያገርሽ ልጅ ነኝ
ቀናቶች ቢበዙ ወራቶችም ቢያልፉ
ለተዋደደ ሰው ትዝታ ነው ትርፉ
እንኳንም በለዛው ቢጠቁርም ቢከሳም
ቁምነገር የሰራ ወዳጅ አይረሳም
ናፍቄ ሳይሽ ክርትት
ዓይኔ ከዓይንሽ ላይ ቅርት
ምን ነካህ በይኝ ቀርበሽ
ባለንጋ ጣትሽ ዳብሰሽ
ፍቅር በኛ ላይ ይንገስ
ያኔ
ቀረብ ፤ ሰብሰብ፤ ለመድ ፤ ወደድ ፤ ጎርደድ
ያንተው ነኝ በይኝ
ከጎንሽ አርጊኝ
ያገርሽ ልጅ ነኝ
ያንተው ነኝ በይኝ
ከጎንሽ አርጊኝ
ያገርሽ ልጅ ነኝ
ያገርሽ ልጅ ነኝ
የወንዝሽ ልጅ ነኘ ኦሆሆ
ያገርሽ ልጅ ነኝ
ያንተው ነኝ በይኝ
ከጎንሽ አርጊኝ አሃሃ
የወንዝሽ ልጅ ነኘ
ያገርሽ ልጅ ነኝ አሃሃ
ከጎንሽ አርጊኝ አሃሃ
የወንዝሽ ልጅ ነኘ
ያገርሽ ልጅ ነኝ አሃሃ
የወንዝሽ ልጅ ነኘ ኦሆሆ
ያገርሽ ልጅ ነኝ አሃሃ
ከጎንሽ አርጊኝ
ያንተው ነኝ በይኝ
የወንዝሽ ልጅ ነኘ
ያገርሽ ልጅ ነኝ
Written by: Tsehay Yohannes
instagramSharePathic_arrow_out