Featured In

Credits

AUSFÜHRENDE KÜNSTLER:INNEN
Gossaye Tesfaye
Gossaye Tesfaye
Künstler:in
KOMPOSITION UND LIEDTEXT
Gossaye Tesfaye
Gossaye Tesfaye
Songwriter:in

Lyrics

የኔን ነገር የትም ለሰው አልነግርም ፍርዱን ለሱ ትቻለው
ሄጄ እሷንም እኔ ለክስ አልጠራም ለዳኛ ብዙ ስላየው
የኔን ነገር የትም ለሰው አልነግርም ፍርዱን ለሱ ትቻለው
ሄጄ እሷንም እኔ ለክስ አልጠራም ለዳኛ ብዙ ስላየው
ዓይኔን ባይኔ አልወጋም ስለተበደለ
አይቶም እንዳላየ ንቆ ማለፍ ሳለ
ምን በወጣኝ እኔ አልሻም ልከሳት
ካለ ሕሊናዋ አያደር ይውቀሳት
ዓይንን ያጎደለ በዳይ ጥፋተኛ
ዓይን ይካስ አይባል እንደ ኦሪት ዳኛ
አደብ ገዝቶ ልቧ ስለኔ ሲገባት
ምነው ትቼው ባልሄድኩ ስትል እንዳልሰማት
ምስክር ካልሆነ ለእውነተኛነቷ
ምን ሊሰራ ዋለ ማህተቡ ካንገቷ
መውደዷን ሲነግረኝ ከዳኝ አንደበቷ
አንደበቷ
ምን ጉድ ነው ምን እዳ
ያመኑት ሲከዳ
ምን ጉድ ነው ምን ቅጣት
ሰው ወዶ ሰው ማጣት
ልቤ በል ተዋት
ማፍቀሬን ካልገባት ካልገባት
የኔን ነገር የትም ለሰው አልነግርም ፍርዱን ለሱ ትቻለው
ሄጄ እሷንም እኔ ለክስ አልጠራም ለዳኛ ብዙ ስላየው
የኔን ነገር የትም ለሰው አልነግርም ፍርዱን ለሱ ትቻለው
ሄጄ እሷንም እኔ ለክስ አልጠራም ለዳኛ ብዙ ስላየው
የደረሰብኝን የውስጤንም ሐዘን
የልቤን ስብራት የጉዳቴን መጠን
እሷም ትየው ብዬ ለሰው አፍ አልሰጣት
እጄን መሰብሰቤ ዝምታዬ ይቅጣት
ዓይንን ያጎደለ በዳይ ጥፋተኛ
ዓይን ይካስ አይባል እንደ ኦሪት ዳኛ
አደብ ገዝቶ ልቧ ስለኔ ሲገባት
ምነው ትቼው ባልሄድኩ ስትል እንዳልሰማት
ምስክር ካልሆነ ለእውነተኛነቷ
ምን ሊሰራ ዋለ ማህተቡ ካንገቷ
መውደዷን ሲነግረኝ ከዳኝ አንደበቷ
አንደበቷ
ምን ጉድ ነው ምን እዳ
ያመኑት ሲከዳ
ምን ጉድ ነው አዬ ምን ቅጣት
ሰው ወዶ ሰው ማጣት
ልቤ በል ተዋት
ማፍቀሬን ካልገባት
በል ተዋት በል ተዋት
Written by: Gossaye Tesfaye
instagramSharePathic_arrow_out