Lyrics

ቀና አታርጉኝ እኔን ከሄደች ትታው መማፀኔን ተክዤ ልግፋው ይህ ሀዘኔን ጨለማ አልብሳው ስትሄድ የፈካው ቀኔን እኔስ አቅም የለኝም እባክሽ ብዬ ልመልሳት ቢፈጀው ልቤን የፍቅር እሳት አይሞከርም መቼም እሷን ለመርሳት ስትሄድ ስለያት ዛሬ ስሰናበታት ማን አወቀልኝ ውስጤን እንደምወዳት ልሸኛት እንጂ የሆዴን ችዬ ባይል ነው ከላይ ግድ የለም ብዬ ገና በጊዜ በቀዬው አድባር አብረን አድገን ክፋት በሌለው በንፁህ ፍቅር ተፈላልገን ተዋደን ኖረን ባልነበር ዓይነት በሚያስቀና ልቧን ከልቤ ድንገት ለያየው ቀን መጣና በደለኛ ሰው ይቅርታ ብሎ አንሶ ሰው ከካሰ ይኖር ወይ ልቡን ያልመለሰ ሳይገባኝ ለኔ የቱጋ እንደሆን እንኳን ማስቀየሜ ተይ ብያት ነበር ባለኝ አቅሜ መማፀኔ ማሪኝ ማለቴ ለኔም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ ታድያ እንዴት ይሆን ወዳጅን መክሮ ልብን መመለስ ወደ ድሮ መማፀኔ ማሪኝ ማለቴ ያውም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ ታድያ እንዴት ይሆን ወዳጅን መክሮ ልብን መመለስ ወደ ድሮ ቀና አታርጉኝ እኔን ከሄደች ትታው መማፀኔን ተክዤ ልግፋው ይህ ሀዘኔን ጨለማ አልብሳው ስትሄድ የፈካው ቀኔን እኔስ አቅም የለኝም እባክሽ ብዬ ልመልሳት ቢፈጀው ልቤን የፍቅር እሳት አይሞከርም መቼም እሷን ለመርሳት ስትሄድ ስለያት ዛሬ ስሰናበታት ማን አወቀልኝ ውስጤን እንደምወዳት ልሸኛት እንጂ የሆዴን ችዬ ባይል ነው ከላይ ግድ የለም ብዬ በዚያ በሚዛን ነፍስ ያለፍቅር መች ይሞላል በሌለሽበት ሲኖር ያላንቺ ቀን ይጎላል እስኪ አውቀንበት ሰው ሳንፈልግ ሌላ ዳኛ ብለን ለፍቅር ተይ እንገናኝ ዞረን እኛ በደለኛ ሰው ይቅርታ ብሎ አንሶ ሰው ከካሰ ይኖር ወይ ልቡን ያልመለሰ ሳይገባኝ ለኔ የቱጋ እንደሆን እንኳን ማስቀየሜ ተይ ብያት ነበር ባለኝ አቅሜ መማፀኔ ማሪኝ ማለቴ ለኔም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ ታድያ እንዴት ይሆን ወዳጅን መክሮ ልብን መመለስ ወደ ድሮ መማፀኔ ማሪኝ ማለቴ ያውም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ ታድያ እንዴት ይሆን ወዳጅን መክሮ ልብን መመለስ ወደ ድሮ
Writer(s): Teddy Afro Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out