Credits
KOMPOSITION UND LIEDTEXT
Michael Belayneh
Songwriter:in
Mesfin Weldetnsaye
Songwriter:in
PRODUKTION UND TECHNIK
Michael Belayneh
Produzent:in
Andy Betezema
Mischtechniker:in
Melaku Sisay
Produzent:in
Lyrics
ካይምሮዬ ጓዳ ቃላት ለቃቅሜ
ከልቤ ማሣ ላይ ስሜቴን ቃርሜ
ብሞክር ልስልሽ ባምጥሽ ባምጥሽ
ስም አልባ ኾነብኝ ረቂቅ ውበትሽ
ረቂቅ ውበትሽ የልቤ ያይኔ ዐዋጅ
የማነሽ እኩያው የማነሽ ተጣማጅ
እንቡጥ ጽጌረዳ የመስከረም ዐደይ
የተስፋ ማለዳው ልጅነት የጸደይ
የዘመን ጌጥ ነሽ ወይ አምሳለ ሰው ዕንቁ
ሲያይሽ እሚጠግብ የሕዝበ አዳም ስንቁ
በሚመጥንሽ ቃል በሚመስልሽ ቀለም
የሚሞክር እንጂ፣ የሚገልጥሽ የለም
ካይምሮዬ ጓዳ ቃላት ለቃቅሜ
ከልቤ ማሣ ላይ ስሜቴን ቃርሜ
ብሞክር ልስልሽ … ባምጥሽ ባምጥሽ
መልክ አልባ ኾነብኝ ረቂቅ ውበትሽ
የማታ ጀምበር ነሽ የሕይወት አመሻሽ
ዓለም በቃኝ ያለሽ ጽድቅ መዳረሻሽ
ወይን ጠጅ ነሽ ወይ የጣዕም ምናኔ
እንዴት የ'ጣሽ ክፋይ አልገባ አልሽኝ እኔ
ቸገረኝ ልብ አጣሁ ልረዳሽ አልቻልኩም
አንቺማ ረቂቅ ነሽ እኔም አልጎበዝኩም
የማነሽ ቅኔ ሰብ የማነሽ ምስጢር
ስንቱ ራሱን ጥሏል ሊያገኝሽ ሲጥር
የማነሽ ትንሣኤ የማነሽ መከራ
ውበትሽ ጸባይሽ ቅኔ ውስጠ ወይራ
ሸማሽ ያገር ባሕል ዘርፉ የባንዲራ
ሙዳየ ቃልኪዳን የእግዜር ድንቅ ሥራ
ፍጹም ውስጠ ወይራ
የእግዜር እጹብ ሥራ
ፍጹም ውስጠ ወይራ
Written by: Mesfin Weldetnsaye, Michael Belayneh, Solomon Sahele