Lyrics

የመልክህን ማማር የሰውነትክን ማማር
ለየቱ ሰሚ ልንገር
ልንገር ልንገር ልንገር ልንገር
ልንገር ልንገር ልንገር ልንገር
የመልክህን ማማር የሰውነትክን ማማር
ለየቱ ሰሚ ልንገር
ልንገር ልንገር ልንገር ልንገር
ለማን ልንገር ያንተን ነገር
አላውቅህ አታውቀኝ በድንገት አይቼህ
መንገዱ ጠፋብኝ ወዴት ልሂድ ትቼህ
ድንገት ሳቅ ስትል ልቤ ደንግጦብኝ
አፍ የፈታሁበት ቋንቋዬም ጠፋብኝ
አንተ ልጅ ውበትህ ትንግርት ነው ታምር
አጊንቼ ባወኩህ እስካመልህ ጭምር
ሰውነትክን ሳስብ በህልሜ ይመጣል በዕውን
ከሀሳቤም ቢሆን አጠፋም ትመጣለህ ባይኔ
የመልክህን ማማር የሰውነትክን ማማር
ለየቱ ሰሚ ልንገር
ልንገር ልንገር ልንገር ልንገር
ልንገር ልንገር ልንገር ልንገር
የመልክህን ማማር የሰውነትክን ማማር
ለየቱ ሰሚ ልንገር
ልንገር ልንገር ልንገር ልንገር
ለማን ልንገር ያንተን ነገር
እንደ ሱፍ አበባ ዛፍ ተመዞ ቁመናህ
ማን ይደርስብሃል አጀብ ነው ቁንጅናህ
ሳቅ ፈገግታህ ሁሉ የሚስጥር ቅመም
ባንድ ቀን ሰጠኸኝ የናፍቆት ህመም
አይቼ እንዳልረሳህ የሆንክብኝ ፍርጃ
መልክህስ ቆንጆ ነው ፀባይህን እንጃ
የግሌ እንዲያረግህ ፀሎቴን አድርሼ
ልቤን ሜዳ ጥዬው መጣው ተመልሼ
አንተ ልጅ ውበትህ ትንግርት ነው ታምር
አጊንቼ ባወኩህ እስካመልህ ጭምር
ሰውነትክን ሳስብ በህልሜ ይመጣል በዕውን
ከሀሳቤም ቢሆን አጠፋም ትመጣለህ ባይኔ
Written by: Dagmawie Ali
instagramSharePathic_arrow_out