Featured In

Credits

AUSFÜHRENDE KÜNSTLER:INNEN
Michael Belayneh
Michael Belayneh
Künstler:in
KOMPOSITION UND LIEDTEXT
Michael Belayneh
Michael Belayneh
Songwriter:in
PRODUKTION UND TECHNIK
Michael Belayneh
Michael Belayneh
Produzent:in

Lyrics

ማልዶ ጎህ መቅደዱ ንጋት ቀርቶ ወጉ
አዕዋፍ አንቀላፉ ዝማሬ ዘነጉ
እርቃን ቀረ ልቤ ባሳብ ቁር ተቀጣ
ቀርጥፎ ሊበላኝ ቤቱም ጥርስ አወጣ
ከማገር ናት ጎጆ ጠረንሽ ቢጠፋ (ጠረንሽ ቢጠፋ)
ሰማይ ሚዛን ሳተ 'ላዬ ላይ ተደፋ
እንደ ምስኪን አሳ ባህር እንደ ከዳው (ባህር እንደ ከዳው)
ብትሄጅ መኖር ጠፋኝ ተጫነኝ ፈተናው
አንቺ የሌለሽ ጊዜ አንቺ የሌለሽ ጊዜ
የቆምኩበት ጠፋኝ ተጫነኝ ትካዜ
አንቺ የሌለሽ ጊዜ አንቺ የሌለሽ ጊዜ
የቆምኩበት ጠፋኝ ተጫነኝ ትካዜ
ማልዶ ጎህ መቅደዱ ንጋት ቀርቶ ወጉ
አዕዋፍ አንቀላፉ ዝማሬ ዘነጉ
እርቃን ቀረ ልቤ ባሳብ ቁር ተቀጣ
ቀርጥፎ ሊበላኝ ቤቱም ጥርስ አወጣ
አንቺ የሌለሽ ጊዜ አንቺ የሌለሽ ጊዜ
የቆምኩበት ጠፋኝ ተጫነኝ ትካዜ
አንቺ የሌለሽ ጊዜ አንቺ የሌለሽ ጊዜ
የቆምኩበት ጠፋኝ ተጫነኝ ትካዜ
ጀንበር ብትወጣ ከኔ ዘንድ የለችም
ብትቀር ገላን እንጂ ልቦናን አትሞቅም
አዳሬ አልተመቸ ውሎዬም አልቀና
ብቸኝነት ፀና
እንቅልፌ ታሞ አይኖቼ ላይ ሞተ
ናፍቆት አንጀቴ ስር ስለቱን ከተተ
በሚዳሰስ ፅልመት ዙርያዬ ታጠረ
ነገር ተሳከረ
አንቺ የሌለሽ ጊዜ አንቺ የሌለሽ ጊዜ
የቆምኩበት ጠፋኝ ተጫነኝ ትካዜ
አንቺ የሌለሽ ጊዜ አንቺ የሌለሽ ጊዜ
የቆምኩበት ጠፋኝ ተጫነኝ ትካዜ
አንቺ የሌለሽ ጊዜ አንቺ የሌለሽ ጊዜ
አንቺ የሌለሽ ጊዜ አንቺ የሌለሽ ጊዜ
አንቺ የሌለሽ ጊዜ አንቺ የሌለሽ ጊዜ
አንቺ የሌለሽ ጊዜ ተጫነኝ ትካዜ
Written by: Michael Belayneh Hailu
instagramSharePathic_arrow_out