Lyrics

እንደ ገብሱ ዛላ የኔ ዓለም ፀጉሯ ተጎንጉኖ
መላው ሰውነቷ የኔ ዓለም በመውደድ ተክኖ
አይነ ኮኮብ ጉብል የኔ ዓለም የደስደስ የዋጣት
አስታውላኝ ሄደች የኔ ዓለም የተዋበች ወጣት
የዘንድሮ ክረምት አጉረመረመና
ሐምሌና ነሐሴ አጥግቦታልና
አሳየኝ ይሄ ዓመት አሄ ያቺን መልከ ቀና
እንዲህም አልነበር ያቻምና ሃሳቤ
እንዲህም አልነበር ያቻምና ሃሳቤ
እንደው በቆንጆ ልጅ አሄ ተጨነቀ ልቤ
ዉበት አይቶ ማለፍ እኔን መች ቸገረኝ
ዉበት አይቶ ማለፍ እኔን መች ቸገረኝ
አሸነፈኝ ቃሏ አሄ ብታነጋግረኝ
እንደ ገብሱ ዛላ የኔ ዓለም ፀጉሯ ተጎንጉኖ
መላው ሰውነቷ የኔ ዓለም በመውደድ ተክኖ
አይነኮኮብ ጉብል የኔ ዓለም የደስደስ የዋጣት
አስታውላኝ ሄደች የኔ ዓለም የተዋበች ወጣት
ሸጋ የለም ብዬ አውነት ነው ተብሎ
ቆንጆ የለም ብዬ እውነት ነው ተብሎ
ጉድ አረገኝ አባይ አሄ ጠምበለል አብቅሎ
ሐምሌና ነሐሴ አልፎ አልቆ ወራቱ
ሐምሌና ነሐሴ አልፎ አልቆ ወራቱ
በጋውም ደረሰ አሄ ተሸኘ ክረምቱ
ያችስ የፍቅር ሰው ምነው ታዲያ አትመጣም
ያችስ የፍቅር ሰው ምነው ታዲያ አትመጣም
እያየ ልበል አሄ ልቤ እየተቀጣም
እንደ ገብሱ ዛላ የኔዓለም ፀጉሯ ተጎንጉኖ
መላው ሰውነቷ የኔዓለም በመውደድ ተክኖ
አይነኮኮብ ጉብል የኔዓለም የደስደስ የዋጣት
አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም የተዋበች ወጣት
ዘመድ ተሰብስቦ ወገን አለኝ ብዬ
ዘመድ ተሰብስቦ ወገን አለኝ ብዬ
ቤቱ ባደስ ደምቆ አሄ ፍርዳየን ጥዬ
ከሰው መጫወቱን ሆዴ እየተመኘ
ከሰው መጫወቱን ሆዴ እየተመኘ
ደሞ ከዳኝ ልቤ አሄ ወደ አንቺው ተሸኘ
አይግጠም ነው እንጅ መቼም ከገጠመ
ልብ እንደ ሁዳዴ እየቆረጠመ
የዞረ ያስፈታል አሄ የተጠመጠመ
እንደ ገብሱ ዛላ የኔዓለም ፀጉሯ ተጎንጉኖ
መላው ሰውነቷ የኔዓለም በመውደድ ተክኖ
አይነኮኮብ ጉብል የኔዓለም የደስደስ የዋጣት
አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም የተዋበች ወጣት
አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም የተዋበች ወጣት
አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም የተዋበች ወጣት
አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም የተዋበች ወጣት
Written by: Elias Woldemariam, Yilma G/Ab
instagramSharePathic_arrow_out