Credits
AUSFÜHRENDE KÜNSTLER:INNEN
Verk
Künstler:in
KOMPOSITION UND LIEDTEXT
Lucas Anhaia
Songwriter:in
Lyrics
አንደኛው ሲክብሽ አንዱ ያፈርስሻል
አንዱ ሲያሳድግሽ አንዱ ይዘርፍሻል
አንዱ ሲሞትልሽ ደግሞ አንዱ ይሾምብሻል
ምንድነው ነገሩ ጥሩ ያልበቀለብሽ
ምንድነው ነገሩ ዘር ያልበቀለብሽ
አንቺ ደሀ ሃገሬ ኢትዮጵያ ዛሬ ማን ያስብሽ
አንቺ ደሀ ሃገሬ እናቴ እስኪ ማን ያስታውስሽ
እስኪ ከራሴ ልጀምር ወቀሳ
ምን ሰራሁ ለሃገሬ ልጠየቅ ልነሳ
እስኪ ሁላችን ያብከንክን ይቆጨን
ከረሃብ ስደት ሌላ ምን ታሪክ አቆየን
አ... ገና ሃገር ማለት ትርጉሙ አልገባንም
አ... የባንዲራ ኩራት ሁኖ አልተረዳንም
አ... እንደ ታሪካችን እንደ ጥንት ቀደምቱ
አ... ላንድነት እንጣር ወገኖቼ በርቱ
ወንዝ እያለሽ አልለማሽም
ልጅ እያለሽ አልተጦርሽም
ውለታሽስ ይኸው ነው ወይ?
ሃገሬ ሰው አጣሽ ወይ?
ሃገሬ አሳቢ አጣሽ ወይ?
ሃገሬ ልጅ አጣሽ ወይ?
ሃገሬ ሰው አጣሽ ወይ?
ሃገሬ አሳቢ አጣሽ ወይ?
ሃገሬ ልጅ አጣሽ ወይ?
አንደኛው ሲክብሽ አንዱ ያፈርስሻል
አንዱ ሲያሳድግሽ አንዱ ይዘርፍሻል
አንዱ ሲሞትልሽ ደግሞ አንዱ ይሾምብሻል
ምንድነው ነገሩ ጥሩ ያልበቀለብሽ
ምንድነው ነገሩ ዘር ያልበቀለብሽ
አንቺ ደሀ ሃገሬ ኢትዮጵያ ዛሬ ማን ያስብሽ
አንቺ ደሀ ሃገሬ እናቴ እስኪ ማን ያስታውስሽ
እስኪ ከራሴ ልጀምር ወቀሳ
ምን ሰራሁ ለሃገሬ ልጠየቅ ልነሳ
እስኪ ሁላችን ያብከንክን ይቆጨን
ከረሃብ ስደት ሌላ ምን ታሪክ አቆየን
አ... አላከበርንሽም ወልደሽ አልተጦርሽም
አ... ወንዝ አለሽ ሃብታም ነሽ አላለማንሽም
አ... አጥፊ ልጆችሽ ነን ይቅር በይ ሰብስቢን
አ... ኢትዮጵያ እናታችን ማሪን አትርገሚን
ወንዝ እያለሽ አልለማሽም
ልጅ እያለሽ አልተጦርሽም
ውለታሽስ ይኸው ነው ወይ?
ሃገሬ ሰው አጣሽ ወይ?
ሃገሬ አሳቢ አጣሽ ወይ?
ሃገሬ ልጅ አጣሽ ወይ?
ሃገሬ ሰው አጣሽ ወይ?
ሃገሬ አሳቢ አጣሽ ወይ?
ሃገሬ ልጅ አጣሽ ወይ?
ሃገሬ ሰው አጣሽ ወይ?
ሃገሬ አሳቢ አጣሽ ወይ?
ሃገሬ ልጅ አጣሽ ወይ?
ሃገሬ ሰው አጣሽ ወይ?
ሃገሬ አሳቢ አጣሽ ወይ?
ሃገሬ ልጅ አጣሽ ወይ?
Lyrics powered by www.musixmatch.com