Top Songs By Veronica Adane
Similar Songs
Credits
AUSFÜHRENDE KÜNSTLER:INNEN
Veronica Adane
Künstler:in
KOMPOSITION UND LIEDTEXT
Eyubel Berhanu
Songwriter:in
Lyrics
ተወደህ እጅ አልሰጥም ባይ
አይሆን ሲሉህ አባባይ
ማርከኸኝ ባንተ ስረታ
አትቅጣኝ ተው በዝምታህ
አይ ተስፋ ይዤበት ገና
ዛሬም ነጋ እንደገና
አፍቅሮኝ እየባዘነ
ልብህ መች ችሎ አመነ
እንደዋዛ ተው ስትፈቀር
ዋ ስትል ሗላ እንዳትቀር
አጉል ኩራትህን ተወት አርግና
ወዷኸኛል እመና ወዷኸኛል እመና
አንተ ሰው ኧረ አንተ ሰው
ኧረ አንተዬ አንተ ሰው
ኩራትህን ቀንሰው ተው
አንተ ሰው ኧረ አንተ ሰው
ኧረ አንተዬ አንተዬ
አለሁ ልብህ ላይ ብታይ
እረ አንተ ሰው
ተው ተው
ሁሌ የት ነሽ ባይ ጠያቂ
ስኖር ሌላዋን ናፋቂ
አይንህ ስሜቱን ያወራል
አፍህ ለምን ይኮራል
አታምንም እንዴ መሸነፍህን በፍቅሬ
አብሬህ ሳለሁ ከጅህ ሳልወጣ ዛሬ
አንዴ ስትቀርበኝ አንዴ ስትሸሸኝ እንደዋዛ
ያንተም ኩራትህ የኔም መንሰፍሰፌ በዛ
አንተ ሰው ኧረ አንተ ሰው
ኧረ አንተዬ አንተ ሰው
ኩራትህን ቀንሰው ተው
አንተዬ አሄ
ካይንህ ስታጣኝ አኩራፊ
አይቶኝ እንዳላየኝ አላፊ
ልብህ ሁሌ እኔን ይልሀል
ብታምን ምን ይልሀል
አታምንም እንዴ መሸነፍህን በፍቅሬ
አብሬህ ሳለሁ ከጅህ ሳልወጣ ዛሬ
አንዴ ስትቀርበኝ አንዴ ስትሸሸኝ እንደዋዛ
ያንተም ኩራትህ የኔም መንሰፍሰፌ በዛ
እንደዋዛ ተው ስትፈቀር (አንተ ሰው)
ዋ ስትል ሗላ እንዳትቀር (እረ አንተ ሰው)
አጉል ኩራትህን ተወት አርግና (እረ አንተዬ)
ወዷኸኛል እመና
ተው ተው ተው ተው
አንተ ሰው (እንደዋዛ ተው ስትፈቀር)
እረ አንተ ሰው (ዋ ስትል ሗላ እንዳትቀር)
እረ አንተዬ አንተ ሰው (አጉል ኩራትህን ተወት አርግና)
ወዷኸኛል እመና
እንደዋዛ ተው ስትፈቀር
ዋ ስትል ሗላ እንዳትቀር (እረ አንተ ሰው)
አጉል ኩራትህን ተወት አርግና
ወዷኸኛል እመና (አንተዬ)
አንተ ሰው ኧረ አንተ ሰው (አንተ ሰው)
ተው ተው ተው ኧረ አንተ ሰው (አንተ ሰው)
አንተ ሰው ተው ተው
Writer(s): Samuel Alemu, Eyubel Berhanu
Lyrics powered by www.musixmatch.com