Lyrics

በሕይወት ፡ ጉዞ ፡ ላይ ቢያደከም ፡ መንገዱ የፈተናው ፡ ብዛት ፡ ዉጣ ፡ ውረዱ ግን ፡ የያዝከው ፡ ተስፋ ከአምላህ ፡ ከጌታ የጰና ፡ ነውና ፡ ወገኔ ፡ በርታ የጰና ፡ ነውና ፡ ወገኔ ፡ በርታ ምናልባትም ፡ በጊዜያዊ ፡ ፈተና ፡ ተጨቀሃል በብዙማ ፡ በብዙ ፡ ሃዘን ፡ በቅሶ ፡ ውስጥ ፡ አልፈሃል ግን ፡ ያሁኑ ፡ የሚያበቃ ፡ የሚያከትም ፡ የሚያልፍ ፡ ነውና ለዘላለም ፡ የፅና ፡ የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለህና አይዞህ ፡ በርታ ፡ ጭክን ፡ በል ፡ በእምነት ፡ ፅና እመጣለሁ ፡ ያለህ ፡ ጌታ ፡ ይመጣልና እመጣለሁ ፡ ያለህ ፡ ጌታ ፡ ይመጣልና በምድር ፡ ላይ ፡ የሰው ፡ ሕይወት ፡ ሰልፍ ፡ ነው ፡ የጦር ፡ ሜዳ ሕይወት ፡ ሩጫ ፡ ለማዘግየት ፡ የሚጥር ፡ የሚጐዳ ጦርነቱን ፡ ለማሸነፍ ፡ ብትፈልግ ፡ ልትረታ አስተውለው ፡ የሰጠህን ፡ ክቡር ፡ ቃል ፡ የአንተ ፡ ጌታ አይዞህ ፡ በርታ ፡ ጭክን ፡ በል ፡ በእምነት ፡ ፅና እመጣለሁ ፡ ያለህ ፡ ጌታ ፡ ይመጣልና እመጣለሁ ፡ ያለህ ፡ ጌታ ፡ ይመጣልና አለኝ ፡ ያልከው ፡ በጅህ ፡ ያለው ፡ ተበትኖ ፡ ቢጠፋ ግራ ፡ ቀኙ ፡ ቢዘጋብህ ፡ ብታጣ ፡ የሚሆን ፡ ተስፋ ሰማያትን ፡ ምድርን ፡ የሰራው ፡ ጌታ ፡ ረዳትህ ብሰማው ፡ ብትፈቅድ ፡ ለአፍታ ፡ ጊዜ ፡ ሰተህ አይዞህ ፡ በርታ ፡ ጭክን ፡ በል ፡ በእምነት ፡ ፅና እመጣለሁ ፡ ያለህ ፡ ጌታ ፡ ይመጣልና እመጣለሁ ፡ ያለህ ፡ ጌታ ፡ ይመጣልና በሕይወት ፡ ጉዞ ፡ ላይ ፡ ቢያደከም ፡ መንገዱ ፡ የፈተናው ፡ ብዛት ፡ ዉጣ ፡ ውረዱ ግን ፡ የያዝከው ፡ ተስፋ ፡ ከአምላህ ፡ ከጌታ የፀና ፡ ነውና ፡ ወገኔ ፡ በርታ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out