Lyrics
እየሱስ መድህኔ
የተጎሳቀለልኝ ለእኔ
ነብሴን ሊያድናት
እርሱ ሆነ መስዋት
እየሱስ መድህኔ
ደሙ ያድናል ደሙ
የመስቀል ላይ ጣሩ ህመሙ
ደሙ ያድናል
ልከፍለው በማልችል እዳ
በሞት ጥሪ ነብሴ ተገዳ
ሳዘግም ወደ ሲኦል መንገድ
ከሰማይ ራርቶልኝ እግዚአብሔር
ውድ እና አንድ ልጁን ላከልኝ
በእኔ ፋንታ እንዲታረድልኝ
ሳይቅማማ መጣ እየሱሴ
አመለጠች ከሲኦል ነብሴ
አለብኝ ውለታው
እየሱስ የከፈለው ብር ወርቅ አይደለም ነብሱን ነው
ተጠምቶ ሲጠጣ መራራ
ሲከፍል የእኔ ስቃይ መከራ
የእሾህ አክሊል ጭኖ በራሱ
ሲጨነቅ እስክታልፍ ነፍሱ
ቀና ብሎ ሲያይ ወደ አባቱ
ጨክኖ አዞሮበት ፊቱን
አንገቱን ደፍቶ ስለእኔ
ተፈፀመ አለ መድህኔ
እየሱስ መድህኔ
የተጎሳቀለልኝ ለእኔ
ነፍሴን ሊያድናት
እርሱ ሆነ መስዋት
ደሙ ያድናል ደሙ
የመስቀል ላይ ጣሩ ስቃዩ ህመሙ
ስለምን ይሆን ይሄ ጌታ
ያጣጣረው በዚያ በጎለጎታ
የተሰደበው የተተፋበት
ባልሰራው ባልፈፀመው ሀጢያት
ለካስ ስለእኔ ነው ቤዛ
ነፍሱን ከፍሎ ነፍሴን የገዛ
ቃል የማይገልፀው ድንቅ ፍጡር
ገለጠልኝ በመስቀል ላይ ጣሩን
አለብኝ ውለታው
እየሱስ የከፈለው ብር ወርቅ አይደለም ነፍሱን ነው
Lyrics powered by www.musixmatch.com